Find Posts By Topic

The City of Seattle can Help Pay Your Electric and Utility Bills

የስያትል ከተማ የኤልክትሪክና የውሃ ግልጋሎት ክፍያዎን ለመክፈል ሊረዳዎት ይችላል።

ኮቪድ-19 በብዙ መንገዶች የስያትል ነዋሪዎችን ጎድቷል። በርካታ ሰዎች በዕድሜ የገፉ አዋቂዎችና ቤተሰቦች ጭምር በሥራ ዕጦት ምክንያት ከባድ የኑሮ ወቅት እየተጋፈጡ ነዉ።

የስያትል ከተማ የኤልክትሪክና የግልጋሎት ክፍያዎችን ለመክፈል የከበዳቸዉን ሰዎች መርዳት ይችላል። ብቁ የሆኑ ነዋሪዎች፡ በስያትል መብራት ሃይልና (Electricity) በስያትል ህዝባዊ ግልጋሎት (Utilities) ክፍያዎች ላይ የ50% ቅናሽ በሚሰጠዉ የስያትል ግልጋሎት ቅናሽ መርሃግብር [ City of Seattle’s Utility Discount Program (UDP)] መመዝገብ ይችላሉ።

ብቁ ለመሆን የቤተሰብዎ ከቀረጥ በፊት ገቢ ከስቴቱ መካከለኛ ገቢ 70% ያህል ወይንም በታች መሆን አለበት። (የ“median income” መጠን በበርካታ መርሃግብሮች ላይ የገቢ ብቁነትን ለመወሰን ጥቅም ላይ ይዉላል። በ 2021፡ አራት ሰዉ ያለበት ቤተሰብ ከቀረጥና ሌሎች ቅናሾች በፊት እስከ $5,996 ድረስ በወር ወይንም $71,952 ዓመታዊ ገቢ ሊኖረዉ ይችላል።)

የ UDP ማመልከቻ ሂደት

  • ይህ ቅጽ በእንግሊዘኛ ነዉ። ለቋንቋ ድጋፍ እባክዎን ተወካይ ለማነጋገር ይደዉሉ።
  • ማመልከቻዎ ታይቶ ዉሳኔ ይሰጥበታል። ማመልከቻዎ የብቁነት መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ ቤተሰብዎ ይመዘገባል።
  • የመልስ ኢሜል ወይንም ደብዳቤ በእንግሊዘኛ ይሆናል።
  • ቅናሹ ክፍያዎችዎ ላይ እስኪታይ እስከ ሁለት የክፍያ ዙሮች ሊወስድ ይችላል።
  • ቅናሹን እንዲያገኙ የጸደቀላቸዉ ደንበኞች ከጸደቀላቸዉ ቀን በኋላ በስድስት ወር የገቢ ሰነድ አቅርበዉ ማመልከቻቸዉን ማሳደስ አለባቸዉ።

ማመልከቻዎን ለማሳደስ ቢሮያችን መገናኘት እንዳለብዎት የሚገልጽ የስልክ ጥሪ፣ ኢሜል እና/ወይም ፖስትካርድ ከተቀበሉ እባክዎን ከተወካይ ጋር ለመነጋገር 206-684-0268 ይደዉሉ። የትርጉም አገልግሎት አለ። ሌላ የኦንላይን ማመልከቻ መሙላት አያስፈልግዎትም።

ስለ UDP ምዝገባ ጥያቄዎች ካለዎት ወይም እርዳታ ከፈለጉ ይደዉሉ ወይም በ UDP@Seatttle.gov ኢሜል ያርጉ። አስተርጓሚ ከፈለጉ እባክዎን ሲደዉሉ ያሳውቁ እና እባክዎን ለየትኛዉ ቋንቋ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ ለኦፕሬተር ይንገሩ። አስተርጓሚ እስኪቀርብ ትንሽ መጠበቅ ይኖርብዎት ይሆናል።

ስለብቁነት ዝርዝር መስፈርቶችን የሚያካትት ተጨማሪ መረጃ ከዚህ ድህረ-ገጽ ማግኘት ይችላሉ፡ www.seattle.gov/UDP

ምንም እንኳን ደንበኞች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ከመክፈል ወደ ኋላ ቀርተዉ ቢሆንም፡ የስያትል መብራት ሃይልና (Electric)፡ የስያትል ፓብሊክ ዩቲሊቲስ (ውሃ) ወረርሽኙ እስካለ ድረስ አገልግሎቶቻቸዉን ለደንበኞች ክፍት እንደሚያደርጉ፡ ከንቲባ ጄኒ ደርኪን አሳውቋል፡ ደንበኞች በቆይታ የመክፈል ዕቅድ በ 206-684-3000 በመደወል ወይም በዚህ ድህረ-ገጽ ኢሜል በመላክ ማሰናዳት ይችላሉ።

Pages: 1 2 3 4 5 6 7